Duration 1:41

The Alibaba group co founder Jack Ma is in Ethiopia, meeting with Ethiopia’s Prime Minister Dr Abiy

24 watched
0
2
Published 26 Nov 2019

ዓለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክ ግብይትን በኢትዮጵያ ማስጀመር የሚያስችል መርሃ ግብር በዛሬው እለት ይፋ ሆነ። ግብይቱን በኢትዮጵያ ማስጀመር የሚያስችለው ስምምነት ከአሊባባ ጋር በዛሬው እለት ተፈርሟል። ስምምነቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ከአሊባባ ተወካይ ጋር ተፈራርመውታል። በስምምነቱ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የዲጂታል ቴክኖሎጅ በበርካታ ዘርፎች እየተስፋፋ መምጣቱን ጠቅሰው፥ ቴክኖሎጂው ከሰው ልጅ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ጋር እየተያያዘ መምጣቱን ተናግረዋል። ቴክኖሎጂው አዳዲስ አሰራሮችን በመተግበር ለሃገራትና ህዝቦች ተጠቃሚነት ከፍ ያለ ድርሻ እንዳለውም ነው የተናገሩት። ቴክኖሎጂ የአኗኗር ዘይቤን በመቀየር ከአሮጌው ወደ አዲሱ መሸጋገሪያ መሆኑንም በንግግራቸው አንስተዋል። ቴክኖሎጂ የአኗኗር ዘይቤን በመቀየር ከአሮጌው ወደ አዲሱ መሸጋገሪያ መሆኑንም በንግግራቸው አንስተዋል። ግብይቱ በታዳጊ ሃገራት የግሉን ዘርፍ ተሳታፊነት በማሳደግ በተለይም ለመካከለኛ ኢንተርፕራይዞች፥ ዓለም አቀፍ የገበያ መረጃዎችን በማድረስ በኩል ተጠቃሚነታቸውን ያሳድጋልም ነው ያሉት። እንዲሁም ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ 10 አመታት ከአፍሪካ በዲጂታል ኢኮኖሚው መስክ ቀዳሚ ከሆኑ 5 ሃገራት መካከል አንዷ ለመሆን የያዘችውን እቅድ ለማሳካት ያግዛልም ነው ያሉት። ከዚህ ባለፈም የግብር ስርዓቱን ቀላልና ግልጽ በማድረግ እና የደንበኞችን ስጋት በመቀነስ አነስተኛ ግብር እንዲኖር እንደሚያግዝም አንስተዋል። የአሊባባ መስራችና ባለቤት ጃክ ማ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ለዲጂታል ቴክኖሎጂው የሰጠችው ትኩረት፥ ዓለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክ ግብይትን በኢትዮጵያ ለማስጀመር እንዳነሳሳቸው ገልጸዋል። ዓለም አቀፉ የኤሌክትሮኒክ ግብይት ኢትዮጵያ የምታመርታቸውን ምርቶች በአሊባባ አማካኝነት በዓለም ገበያ ግብይት እንድትፈፅም የሚያስችል ነው ተብሏል።

Category

Show more

Comments - 0